የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“‎ዛሬ ያስጀመርነው የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ የበቆሎ እና ማሽላ ዱቄት እንዲሁም 14 ተጓዳኝ የበቆሎ ውጤት ምርቶችን ለማምረት የታቀደ ነው። ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲግባ በቀን 2000 ቶን በቆሎ እና 120 ቶን ማሽላ የማምረት አቅም ይኖረዋል።

ከ6500 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል የሚፈጥር ሲሆን ለአካባቢው አርሶአደሮች፣ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እና የግል ዘርፍ አምራቾች የእሴት ሰንሰለትን በማገዝ ለአካባቢው አርሶአደሮች ሰፊ ገበያ ይፈጥራል፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ያሳድጋል።”

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts