የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“ዛሬ በታሪካዊው የሀገራዊ ምክክራችን ዋዜማ፣ የኢትዮጵያ ታላቅ ወዳጅ የሆኑትን ክቡር ኦሊሴጉን ኦባሳንጆን በጽሕፈት ቤቴ ተቀብያለሁ። በመጪው ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ለመወያየት እንዲሁም ከዚህ ቀደም ካከናወኗቸው ተግባራት ጥበብ ለመቅሰም ችለናል፤ በተለይም የቢያፍራን የሰላም ሂደት በመምራት ያካበቱትን ልምድ አጋርተውናል። ይህም ኢትዮጵያ በምክክር ለምታረጋግጠው አንድነትና ዘላቂ የሰላም ጉዞ ላይ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ ነው።

ኢትዮጵያ ለምታበረክቱት በዋጋ የማይተመን አስተዋጽኦ ሁልጊዜም የላቀ ምስጋናዋን ታቀርባለች! “

Similar Posts