ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ ችግኞችን ተከሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር በመሆን በጫካ ፕሮጀክት ስፍራ ሀገር በቀል የአረንጓዴ አሻራ ችግኞችን ተክለዋል።
የባህር ዛፍን በሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች የመተካቱ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዓሻራ መርሃ ግብር ሁሉም ዜጋ ተካፋይ እንዲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቀርበዋል::
