ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እድሳት የተደረገለትን የፋሲል ግቢ በሚመርቁ ወቅት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የጎንደር ህዝብ ታላቅ በሆነው በዚህ ደስታው ተካፋይ እንድንሆን ስለፈቀደልን እናመሰግናለን ።
ጎንደር ሽማግሌዎች አሏት ባዕድ ሳይሆን ባላገሮች፣ ባለቤቶች እንኳን ከአንድ ሰፈር ወደ ሌላ ሰፈር ተንቀሳቅሰው የሀገራቸውን ልማት ማየት፣ ማገዝ እንዲችሉ ሰላም ያስፈልጋል ።
የወጡ ወንድሞቻችን ጊዜ ማባከን የለባቸውም፤ የሚያስፈልገን ተመልሰው በአንድነት እና በትብብር መሥራት፣ ሀገር ማልማት አለብን ።
ዛሬ ጎንደርን፣ ባሕርዳርን ወይም አማራ ክልልን ከአማራ ተወላጆች በስተቀር ማንም አያዝበትም ።
እኛ የክልሉን ልማት ከማገዝ በቀር በዕለት ተዕለት ጉዳይ እና ሥራዎች ውስጥ እጃችንን አናስገባም ። ይህ ዕድል ኢትዮጵያ ውስጥ አልነበረም ፤ አሁንም ይህን ዕድል ከምናበላሸው በትብብር መንፈስ ብንሠራ የገራአችን፣ የልጆቻችን ነገ ያማረ ይሆናል ።
ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ ዳግም እንዲወለዱ በትብብር መንፈስ በጋራ እንድንቆም አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ
የፋሲል ቤተመንግሥት ዕድሳትን በተመለከተ
ይህን የመሰለ ስጦታ የሰጡን አባቶቻችን የነሱን ፈለግ ተከትለን ሀገር ብናለማ ሀገር ብንሰራ ዛሬ ኢትዮጵያ ተረጂ አትሆንም ነበር ።
የታላቆችን ስራ ማድነቅ፣ ማክበር እና መመርመር መጀመር ለዛ ስራ አንድ ጡብ ወደ ማስቀመጥ ያሸጋግራል ።
ትናንትናችን ማስታወሻችን መታወሻችን በመሆኑ ሰው ማስታወሻውን መታወሻውን አይዘነጋም። ኋላውን ማስታወስ የቻለ ሰው እና ማህበረሰብ ዛሬን ለመነሻነት እና ለመስሪያነት ይገለገላል ።
በጎንደር ከተማ የተጀመሩ ስራዎች እና በፋሲል ቤተ መንግስት ግቢ ውስጥ የታየው ለውጥ ልጆቻን ከኛ የተሻለ ተስፋ እንዳላቸው ማሰብ ብቻ ሳይሆን በሚጨበጥ ነገር ለማየት ያስችላል።
የጎንደር ልጆች አባቶች ያስረከቡትን እና ዛሬ የተሰራውን ስራ የበለጠ በሚያልቅ መልኩ በመስራት የበለጠ ያማረ፣ የተዋበ እና የለማ ሀገር ለመፍጠር ሥሩ ።
ፋሲል ቤተ መንግስት መጠገን እና መታደስ ብቻ ዳግም ነው የተወለደው ።
እንደ ፋሲል ዳግም ውልደት ሁሉ ጎንደር ዳግም እንድትወለድ የሁላችንም መሻት እና ስራ ሊሆን ይገባል ።
ጎንደር ዳግም ተወልዳ ለዓለም አሸብራቂ ከተማ እስክትሆን ድረስ ሁላችንመ በጋራና በትጋት እንሥራ ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)



