በሀገሪቱ ያለፉ ቁርሾዎችንና ስብራቶችን የሚጠግን፣ በትብብር ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ባህልን የሚያጎለብት መደላድል እየተፈጠረ ነው
የሰላምን አማራጭ የተከተሉ የትኞቹም ቡድኖች በሀገረ መንግሥት ግንባታ ጥረት በንቃት እንዲሳተፉና የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ጽኑ ፍላጎት አለው ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ። ለሰላም አዎንታዊ ምላሽ የሰጡ የቀድሞ ታጣቂዎች ሀገሪቱ በያዘችው የሰላምና የብልጽግና ጉዞ ሂደት ውስጥ ሊጫወቱ የሚችሉትን ወሳኝ ሚና መንግሥት ይገነዘባል ብለዋል ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)። የሰላም አማራጭን…