ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የኢትዮጵያ ብዝኃነት ማሳያ ናቸው!
************************** የመስቀል ደመራ በዓል ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው መካከል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ በመላው ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወራረሰ እና ተጠብቆ የቀጠለ ክዋኔን የሚያሳይ የኢትዮጵያ ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበዉም ይህንን ነባር የአከባበር ትውፊቱን ይዞ እንዲቀጥል፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የሰው ልጆች ኹሉ…
