የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን እና የኢትዮጵያዊያንን ዉበት የሚያጎላ ነው፡
ኢትዮጵያ የብዝኃ ቋንቋ፣ ብዝኃ ባህልና ብዝኃ ማንነት ሃገር ናት፡፡ ብዝኃነት ለኢትዮጵያዊያን ተፈጥሯችን፣ ዉበታችንና የጥንካሬአችን ምንጭ ነው፡፡ ብዝኃ ማንነት ያለበት ሕዝቦች ሀገር መሆናችን ጸጋችን ነው፤ ብዝኃነት የኢትዮጵያ ተጨባጭ እዉነታና ውብትም ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሂደት አንድ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት በርካታ መንገዶች ተሞክሯል፡፡ ነባሩንና ተፈጥሯችን የሆነውን ብዝኃ ማንነትን በአንድ ወጥ ማንነት ለመቀየር ብዙ ተለፍቶበታል፡፡ በፖሊሲና ተቋማዊ አሰራር…