1ኛው የአፍሪካ የከተሞች ፎረም ሁለተኛው ቀን ውሎው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀችው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም “ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063” በዓድዋ መታሰቢያ ፓን-አፍሪካን አዳራሽ በሁለተኛ ቀን ውሎው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እየመከረ ነው፡፡ በፎረሙ ላይ የተባበሩት መንግስታት የሥራ ኃላፊች፣ የዓለም ዓቀፍ የልማት ድርጅቶች፣ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎችና የተቋማት ኃላፊዎች፣ የአፍሪካ ከተማ ከንቲባዎች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሥራ ኃላፊዎች፣ የግሉ ሴክተር አንቀሳቃሾች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት…
