ኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ ተዘጋጅታልች
በኢትዮጵያ የጂኦ-ቱሪዝም እምቅ ሀብቶቿን በዩኔስኮ ዓለም አቀፍ የጂኦ-ፓርክነት በማስመዝገብ ተጠቃሚነቷን ለማሳደግ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ። ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላት ያልተነካ ሀብት በጂኦ-ቱሪዝም ተመራጭ ሀገር የሚያድርጋት ነው። ከዚህ አንጻር ለዩኔስኮ በወደፊቱ ሊቀርቡ የሚችሉ በርካታ የሀገሪቱ እጩ የጂኦ-ቅርስ ቦታዎች ተለይተዋል። ከነዚህም ውስጥ በባሌ ወረዳ የሚገኘው ሶፍ-ዑመር ዋሻ፣ በቡታጅራ-ስልጤ የሚገኙት አፈጣጠሮች፣ የሰሜንና የገራልታ ተራሮች፣ የደናክል ስምጥ ሸለቆ፣ ኤርታ…
