የዲጂታል ትምህርት
ኢትዮጵያ ተማሪዎችና ወጣቶች በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርትና ክህሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የዲጂታል ስርዓት ትምህርትን በዋነኛነት እያስፋፋች ትገኛለች። የኢንተርኔት ትስስር መንገዶቸን በማመቻቸት እንዲሁም የዲጂታል መሣሪያዎችን እና የኢ-ለርኒንግ (E-learning) ግብዓቶችን በትምህርት ቤቶችና በስልጠና ማዕከላት ውስጥ በማካተት እነዚህ መርሃ ግብሮች የመማር ዕድሎችን ያሰፋሉ፤ የትምህርት ክፍተቶችን ይደፍናሉ፤ እንዲሁም ተማሪዎችን ለዘመናዊው የሥራ ዓለም ዝግጁ ያደርጋሉ። ዲጂታል ትምህርት ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ፣ በችግር አፈታት እና…
