መንግሥት ቃልን በተግባር በመግለጽ የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እያሳካ ነው!

*************************** መንግሥት ከለውጡ እውን መሆን ጀምሮ የገባቸዉን ቃሎች እየፈጸመ፣ ኢትዮጵያን ወደሚገባት ከፍታ ለማውጣት የብልጽግና ጉዞዉን እያሳመረ ቀጥሏል፡፡ ከዓመታት በፊት በ2018 ዓ.ም ከተስፋ ብርሃን ወደሚጨበጥ ብርሃን ሽግግር እናደርጋለን የሚል የሚል ርዕይ የያዘው ቃል የኢፌዴሪ መንግሥት ቃሉን በተግባር እየገለጸ ይገኛል፡፡ የምግብ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ ብዙ ርቀት ተጉዘናል፤ በመኸር እርሻ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በበጋ መስኖ በመታገዝ ሰፋፊ…

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምስራቋ ጮራ ጅግጅጋ ከተማ ሲደርሱ የተደረገላቸው አቀባበል

https://web.facebook.com/share/v/174RoV6wpD

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር የዕውቅና እና የምስጋና ስጦታ አበረከተ፡፡

መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ/ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለኢፌዴሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር በ2017 ዓ/ም ጉባኤው የሠራቸውን የሰላም እና ማሕበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች ለሕዝብ በስፋት ተደራሽ ይሆኑ ዘንድ በቂ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ላበረከተው ሁሉን አቀፍ አገልግሎት በዛሬው ዕለት የዕውቅና እና የምስጋና ስጦታ በክብር አበርክቷል፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸኃፊ ሊቀ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ጥበቃ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን ጨምሮ ሰፊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። ውይይቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ምንጭ የሚውል የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ የማልማት ስምምነቶችን ጨምሮ የጋራ ፍላጎት በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተካሂዷል። Prime Minister Abiy Ahmed held talks with President Vladimir Putin on a…

ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የኢትዮጵያ ብዝኃነት ማሳያ ናቸው!

************************** የመስቀል ደመራ በዓል ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው መካከል አንዱ ነው፡፡ በዓሉ በመላው ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወራረሰ እና ተጠብቆ የቀጠለ ክዋኔን የሚያሳይ የኢትዮጵያ ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ ነው፡፡ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበዉም ይህንን ነባር የአከባበር ትውፊቱን ይዞ እንዲቀጥል፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የሰው ልጆች ኹሉ…

ክብርት እናትዓለም መለሰ በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

መስከረም 09 ቀን 2018 ዓ.ም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር በመኾን የተሾሙት ክብርት እናትዓለም መለሰ ዛሬ በአገልግሎቱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ከአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋርም ትውውቅ አድርገዋል፡፡ *************

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አደረገ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ለክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በእስካሁኑ ለተቋሙ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የምስጋና እና የሽኝት መረሃ ግብር አድርጓል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በመረሃግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ክቡር አምባሳደር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተቋሙ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አሻራ ማስቀመጣቸዉን ገልጸዋል፡፡ አገልግሎቱ በ2014 ዓ.ም እንደ አዲስ ሲመሰረት ከምንም በመነሳት…

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ (ዶር) አራተኛውን “የመደመር መንግስት”  የተሰኘዉን መጽሐፍ አስመረቁ

መስከረም 6/2017 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  አሕመድ(ዶር) አራተኛውን “የመደመር መንግስት”  የተሰኘዉን መጽሐፍ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬክሽን ማዕከል በትላንትናው ዕለት በይፋ አስመርቀዋል፡፡ አድሱ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ ዉስጥ የተገኙ ሁሉ አቀፍ ዉጤቶችና ተግዳሮቶች፣ እድሎችና ስጋቶች፣ እንዲሁም ተጨባጭ መፍትሔዎችን በማቅረብ የመደመር ፍልስፍናን በጥልቀት የሚተነትን ነዉ፡፡ በተለይም መጽሐፉ በዲጂታል ኢትዮጵያ የታገዘ ቀልጣፋ የህዝብ አስተዳደር ገጽታ፣ ሀገራዊ አንድነት እና…

ኢትዮጵያ ለማንሰራራት የሚስችላትን ከፍታ ይዛለች!

ኢትዮጵያ በሚመጥናት ከፍታ ልክ የሚያስቀምጣትን የማንሰራራት ጉዞ ጀምራለች፡፡ በጊዜ ምሕዋር ውስጥ ሲያጋጥሟት የነበሩ አንጋዳዎችን በብስለት እየተሻገረች ከፍታዋን በመያዝ ላይ ናት፡፡ የአይችሉም ትርክትን በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሰብራለች፤ ብርሃንን ለምሥራቅ አፍሪካ ፈንጥቃለች፡፡ ያለማንም ዕርዳታ በኢትዮጵያውያን ሀብት፣ ድካም፣ ዕውቀትና ጥረት ሕዳሴን በማጠናቀቅ ኢንዱስትሪዎቿን በበቂ ታዳሽ ኃይል የምታንቀሳቀስ፣ ከዚያም አልፎ ለጎረቤት አገራት የምታጋራ ኾናለች፡፡ በውኃ ሀብቶቿ በፍትሐዊነት በመጠቀም ዐዲስ…

ኢትዮጵያ የምታስተናግደዉ 2ኛው የአፍሪካ አየር ንብረት ጉባዔ ሀገራችን ያሳካቻቸው ተጨባጭ ልምዶችን የምታካፍልበት መድረክ ነው፡:

********************************* 2ኛዉ የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን ጉባኤ የምታስተናግደዉ ለተሳታፊዎች ተጨባጭ ልምዶችን በማካፈል ጭምር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እየሠራች ትገኛለች፡፡ መላዉ ኢትዮጵያውያን በተከታታይ ዓመት በሚያደርጉት የላቀ ተሳትፎ የራሳቸዉን ክብረ ወሰን እያሻሻሉ በአንድ ጀምበር ከ700 ሚሊዮን በላይ…