የንግድ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበርና ለትውልድ የሚሻገሩ የልማት ሥራዎችን አጀንዳ አድርጎ መስራት ይጠበቅባቸዋል – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የንግድ ሚዲያዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበርና ለትውልድ የሚሻገሩ ሀገራዊ የልማት ሥራዎችን አጀንዳ አድርጎ በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ። መንግስት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከንግድ ሚዲያዎች ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገልጿል። መንግሥትና የንግድ ሚዲያዎች በሀገር ግንባታ ሥራዎች ላይ ይበልጥ ተቀራርበው መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ ተካሂዷል። በሀገራዊ ለውጥ ጉዞ የተገኙ ስኬቶችን ማሳወቅ፣ የገጠሙ…
