ኢትዮጵያ የብዝሃ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በመከተሏ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ተመዝግቧል _ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕዝብ ተወካዎች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሳባ ላይ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኢኮኖሚው ዘርፍ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ኢትዮጵያ የብዝሃ የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመከተሏ ዘርፈ ብዙ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከዚህ ቀደም ግብርና መር የነበረው፣ አሁን ግብርናን ጨምሮ በማኑፋክቸሪንግ ፣በማዕድን፣ በቱሪዝም ፣በእንዱስትሪ እና በተክኖሎጂ…

