በመገጭ የመስኖ ፕሮጀክት የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ ።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሙሉ መልዕክት :- “በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል። ፕሮጀክቱ 870 ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን 17000 ሄክታር መሬት በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል። የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። የቀሩት ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ ይገኛሉ። የመገጭ ግድብም በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት…

