ምስጋና ይገባቸዋል
“የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ” የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከማለዳው12 ሰአት ጀምሮ እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት በመላ ሃገሪቱ ሲካሄድ ለኢትዮጵያዊያንና ለመላው ዓለም መረጃውን ለማድረስ በከፍተኛ ትጋት ኃላፊነታችሁን ለተወጣችሁ የመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላቅ ያለ ምሥጋናውን ያቀርባል፡፡ ሰላማዊት ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ በዚህ ለአንድ ቀን በተካሄደው የአንድ…
ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል።
የዛሬ ጀምበር ወጥታ እስክትጠልቅ ስድስት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ልንተክል ኢትዮጵያውያን ሁሉ አቅደን ነበር። ያሰብነውን ሳናሳካ ጀምበር የሚጠልቅብን አይደለንምና በአንድ ጀምበር 615.7 ሚሊዮን ችግኞችን መትከል ችለናል። ህፃናት ተስፋቸውን ተክለዋል። ወጣቶች ጽናተቸውን አሳይተዋል። አረጋውያን ውርስ አኑረዋል። ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከቤታቸው ወጥተው የማይደበዝዝ አሻራ አኑረዋል። በማበራችን እና በመጽናታችን በአለም በሌላ ስፍራ በአንድ ጀምበር ያልተደረገውን እኛ ኢትዮጵያውያን አድርገነዋል።…
ኢትዮጵያ እየተከለች ነዉ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ (ዶ.ር) በአንድ ጀንበር #600_ሚሊየን_ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ላይ አሻራቸዉን አሳረፉ።
ኑ ታሪክ እንስራ !
በዛሬዉ እለት ኢትዮጵያዊያን ታሪክ ለመስራት ከጫፍ ጫፍ በነቂስ እየወጡ ነዉ፡፡ ከብረት በጠነከረዉ አንድነታችን ዘር ፣ ቀለም ፣ ሀይማኖት ፣ እድሜ ፣ ፆታ ሳይለየዉ ወርቃማ ታሪክ ለማስመዝገብ አንድ ብለን ጀምረናል። በዛሬዉ እለት በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል የአንድነታችን ሃይል ደምቆ ይታያል፡፡ እኛ አትዮያዊያን በአንድነት ተነስተን ፣ በህብረት ተባብረን ፣ በአንድ ጀምበር 600 ሚለዮን ችግኝ በመትከል…
የ”አምስት ሚሊዮን ኮደርስ” ነፃ የስልጠና ፕሮግራም ተሳታፊ ለመሆን ከታች ያለዉን ማስፈንጠሪያ ( Link )በመጠቀም መመዝገብ እና ስልጠና መዉሰድ ይችላሉ::
Link :- https://ethiocoders.et/
“በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
<< ነሐሴ 17፣ 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር::በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር፡፡ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን!አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊወች ከ10 በላይ በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ፡፡Hagayya 17/2016 guyyaa tokkotti biqilruuwwan miliyoona 600 dhaabuudhaan ashaaraa keenya haa keewwannu.Guutummaa Itoophiyaatti qalbii tokkoon ashaaraa keenya haa…
“የመገናኛ ብዙኃን የተረጂነት አስተሳሰብን በመለወጥ ዜጎች ሰርቶ መለወጥ እንደሚቻል ተረጂነት ሃገራዊ ክብርንም የሚነካ መሆኑን በማስረዳትና ግንዛቤ በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ኃላፊነት ተጥሎባችኋል፡፡”
ሰላማዊት ካሳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ፖሊሲ ላይ ለሁለት ቀናት የተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ሚኒስትር ዴኤታዋ እንዳሉት የሰብአዊ ድጋፍ ጠባቂነት አመለካከትን መየቀር የመገናኛ ብዙኃንና የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ኃላፊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም፣ሐብት ያላት ሃገር ናት ያሉት ሰላማዊት ካሳ…
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምክንያት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም ብለዋል።
ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ በመግለጫቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ተከታዩቹ ይገኙበታል። ማሻሻያው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ የሁለተኛው መካከለኛ ዘመን መርሃ ግብር ምሰሶ የሆኑ አራቱን መሰረታዊ ጉዳዮች ማለትም፦ 1) በሀገሪቱ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን መፍጠር 2) የንግድ ስራዎችን የሚያሳልጡ የሚያቃልሉና ውጤታማነትን የሚያሻሽሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ከባቢን ማሻሻል 3) የዘርፎቹች ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን የማሳደግ እና የመንግስት የማስፈጸም አቅምን…
