የፕሬስ መግለጫ
ኢትዮጵያዊነት ብያኔዉ የተሻለ ዓልሞ የላቀ ማሳካት ነው! ኢትዮጵያ የቀደምት ሥልጣኔ መነሻ፣ የጥቍር ሕዝቦች የነፃነት ቀንዲል ብቻ አይደለችም፤ ኢትዮጵያ የመጪዉ ትውልድ የተስፋ ምድር ጭምር ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በጋራ ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር የሚገለጹ፣ የመቻል ተምሳሌቶች ናቸው፡፡ “በጋራ እንችላለን” ብለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን እውን አደረጉ፡፡ “በጋራ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እናልብስ” ብለው ላለፉት ስድስት ዓመታት ከ40 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን…