Similar Posts
በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ የታዛቢዎች እይታ
የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች የኢትዮጵያን 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አዎንታዊና ሕጋዊ ማዕቀፉን የተከተለ እንደነበር በመግለፅ ፤ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሰራውን ሥራ አበረታተዋል ። በቀጣይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ቅሬታዎቻቸውን በሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ፣ የሴቶች ተሳትፎና የውይይት ባህል ይበልጥ እንዲጎለብት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳያቸውን በራሳቸው እንዲወስኑ ዕድል እንዲሰጥ አሳስበዋል። ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች…
በአንድ ጀምበር ሚሊዮኖችን በመትከል የማንሰራራት ታሪካዊ ጉዞ አካል እንሁን!
ኢትዮጵያን ወደ ነበራት ጥንታዊ የደን ሽፋን በመመለስ አረንጓዴ ካባ ለማልበስ የጀመርነው ጥረት 7ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል፤ 7ኛ ዓመት የጥረታችንን ጅማሮ የምንዘክረዉ ደግሞ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ነው፡፡ ባለፉት 6 ዓመታት የአረንጓዴ ዐሻራ ጉዟችን ኢትዮጵያውያን ከሁሉም አቅጣጫ፣ ከደጋ እስከ ቆላ በጋራ ባደረግነዉ ጥረት 40 ቢሊዮን ችግኞች በላይ ተክለናል፤ የኢትዮጵያን የደን ሽፋንም እስከ ባለፈዉ ዓመት…
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየሠራን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤን ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል!
ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጀመረቻቸዉ ጥረቶች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል፤ ለላቀ ስኬትም ጥረቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ በዚህ ወሳኝ ወቅት ኢትዮጵያ ከጣልያን መንግሥት እና ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በመቀናጀት 2ኛዉን የዓለም የምግብ ሥርዐት ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡ ይህም በኹለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ውስጥ ኢትዮጵያ እየተጫወተች ያለዉን ሚና የሚጎላ፣ በሥርዐተ ምግብ ዙሪያ የጀመረቻቸዉን ስኬታማ ተግባራት የሚያበረታታ ነው፡፡ ከዐራት ዓመታት…
ሀገራዊ የልማት እቅዱ የተገኙ እምርታዊ ዉጤቶችን የሚያስቀጥልና የተደመረ አቅምን የሚፈጥር ነዉ- ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
የ2018 ሀገራዊ የልማት አቅድ በሁሉም ዘርፎች የተገኙ እምርታዊ ዉጤቶችን የሚያስቀጥልና ለላቀ ዉጤት የተደመረ አቅም የሚፈጥር እቅድ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የአገልግሎቱ አመራርና ሰራተኞችም በእቅዱ ላይ ዛሬ ዉይይት አድርገዋል፡፡ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ሀገራዊ እቅዱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም በሁሉም ዘርፎች ያስመዘገበችዉ የኢኮኖሚ እድገት እምርታ የታየበት መሆኑን…
ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋን እንዲዘጋ ወሰነች
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመዝጋት መወሰኑን አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ በኩል ለተሰነዘሩ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ላልሆኑ ጠብ ጫሪ እና የጠላትነት ድርጊቶች የአጸፋ ምላሽ በመስጠት፣ በኤርትራ አስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲውን ለመዝጋት ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል። ሚኒስቴሩ አያይዞም የቪዬና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነት ድንጋጌዎችን በመጣስ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ቀጥተኛ አደጋ በሚፈጥሩ…
