የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“የቡሩንዲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ክቡር ኤቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ፤ በድንቅ ህዝቦቿና ባህሏ ወደ ምትቀበሎት ሀገሬ ኢትዮጵያ እንኳን በሰላም መጡ ስል በታላቅ ክብር ነው። ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ ጥልቅ የሆነ የወንድማማችነት እና የጋራ መከባበር ታሪክ ያላቸው ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘላቂ ትስስርም በከፍተኛ ሁኔታ እንደምናከብር ላስታውሶት እወዳለሁ። በዚህ ይፋዊ የስራ ጉብኝትዎ፣ ለወደፊቱ ያለንን የጋራ ትልም ወደ እውነት ለመቀየር በምናደርገው ጥረት፤ ቆይታዎ ግንኙነታችንን የበለጠ እንደሚያጠናክረው አልጠራጠርም። በድጋሚ እንኳን ወደ ሁለተኛ ቤትዎ በደህና መጡ ለማለት እወዳለሁ!”

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts