በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚታየው የእሴት ሰንሰለትን በተመለከተ !
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚታየው የእሴት ሰንሰለት በበርካታ ሁኔታዎች የሚገለጽ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የዘርፉ እንቅስቃሴዎች ነገ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ በእርግጠኝነት መተንበይ የማይቻልበት ዓለም አቀፋዊ ተጨባጭ ሁኔታ ተፈጥሯል።
በተለይም የተለያዩ አገራት የራሳቸውን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ሲሉ በሌሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ የንግድ ውጥረቶች እንዲፈጠሩ የሚያደርጉበት አጋጣሚ መኖሩን መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህም በዓለም አቀፍ የንግድ መስተጋብር ውስጥ እርግጠኝነትን በማጥፋት በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
የታሪፍ ዋጋን ያለአግባብ መጨመር፣ የወጪና ገቢ ምርቶች ላይ ገደብ መጣል፣ እንዲሁም በባሕር የንግድ መስመሮች ላይ የሚደረጉ ትንኮሳዎች ለዘርፉ መስተጓጎል በምክንያትነት የሚጠቀሱ ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች ናቸው።
ከእነዚህም በተጨማሪ ያልታሰቡ ወረርሽኞች እና መልክዓ-ምድራዊ ፉክክሮች መከሰታቸው በሀገራት መካከል ያለውን የንግድና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመጉዳት፣ ቀደም ሲል የነበረው ጤናማ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲሻክርና ውጥረት ውስጥ እንዲገባ እያደረገው ነው።
በመሆኑም አሁን የሚታየው ማንኛውም ሁኔታ ነገ ሊቀየር ስለሚችል፣ የወደፊቱን ሁኔታ አስቀድሞ በማጤንና የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ማዕከል ያደረገ ውሳኔ ማሳለፍ ውጤታማ እንደሚያደርግ መገንዘብ ይገባል። ዛሬ ላይ ያለው ሁኔታ ነገ ላይቀጥል እንደሚችል በመረዳት፣ መንግሥት የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ለማስጠበቅ በትኩረት እየሠራ ይገኛል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

