ዓለምን በሚበይነው የዲጂታል ዘርፍ ሪፎርም የተገኙ ቁልፍ ውጤቶች:-
• መሰረተ-ልማት-
የ5G እና የ4G ሽፋን መስፋፋት።
• የዲጂታል መሳሪያዎች-
ስማርት ስልኮችን በሀገር ውስጥ መገጣጠም።
• ዲጂታል መንግስት-
በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት 2260 አገልግሎቶች በአንድ ቋት መደራጀት፣ ዲጂታል ክፍያዎች፣ የፍትህ ተደራሽ ስማርት ችሎት እና ዲጂታል ፖሊስ።
• ዲጂታል ክህሎት-
5 ሚሊዮን ኮደሮች ስልጠና፣ ትምህርት ቤቶችን በኢንተርኔት (SchoolNet)፣ በሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ደረጃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ምርምር እና ስታርት አፖችን በእውቀትና በፈጠራ ማብቃት።
• የተቋማት ግንባታ-
ዲጂታል ስታቲስቲክስ እና ልማት አስተዳደር፣ AI ኢንስቲትዩት፣ AI ዩኒቨርሲቲ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር።
• የህግ ማዕቀፍ ተዓማኒነት-
በፋይዳ መታወቂያ ከ40.9 ሚሊዮን በላይ ዜጋ ተካቷል፣ የግል መረጃ ጥበቃ አዋጅ፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ተግባራዊነት።
PMOEthiopia #DigitalEthiopia2030 #EthiopiaDelivers

