የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
”የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ተገኝቼ ሃሳቤን አጋርቻለው።
የማህበራዊ ዘርፍ ግንባታ እንደ ሌሎች መሠረተ-ልማቶች ውጤቱ ወዲያው የሚታይና የሚጨበጥ ባይሆንም፣ ለሀገር ዘላቂና ወሳኝ መሰረት የሚጥል ነው። ኢትዮጵያ በሚገጥሟት ተግዳሮቶች ሳትገደብ ከሚገመተው በላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተገነባች ሲሆን፣ ምንም እንኳ የዐቅም ውስንነቶች ቢኖሩብንም ለማሻሻል ያልተሞከረ የማህበራዊ ዘርፍ የለም።
በዘርፎች የታለመው ሁሉ በተግባር እንዲተረጎምና ተገቢውን ዓላማቸውን እንዲያሳኩ ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል። ስለሆነም አንድ እጅ ብቻውን ማጨብጨብ አንደማይችል ሁሉ፤ መንግሥት የሚጀምራቸውን ሥራዎች ሌላው የማህበረሰብ ክፍል እንደ አንድ ባለ ድርሻ ኃላፊነት ወስዶ በጋራ መቆም ይኖርብናል።”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች: https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication





