አራዳ ፓርክ
ይኽ በአዲስ አበባ እምብርት የሚገኝ የከተማ ውስጥ ድንቅ የሕዝብ መገልገያ ሲሆን በሁሉም እድሜ እና ማኅበራዊ ሁኔታ ያሉ ሰዎች በጋራ የሚሰበሰቡበት፣ የሚዝናኑበት፣ ጽዱ እና ደማቅ አድርገው በመጠበቅም ተሚኮሩበት ስፍራ ነው። 40 ሄክታር መሬት ላይ ካረፈው ፓርክ 15 ሄክታሩ በለምለም አረንጓዴ መስክ የተሰናዳ ሲሆን 6 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 5 ኪሎሜትር የብስክሌትና መሮጫ ትራክ የተዘጋጀለትም ነው። ይኽም ንቁ እና ጤናማ አኗኗርን የሚያበረታታ ነው። በፓርኩ 131 ሱቆች፣ ካፌዎች፣ የአገልግሎት መስጫዎች፣ የስፖርት እና የባሕል እና ጥበባት መከወኛዎች፣ እንደየሕፃናት መጫወቻ እና አነስተኛ የሕፃናት ከተማ ያሉ የቤተሰብ መዝናኛዎች ይገኛሉ። ሁሉም በፓርኩ በሚገኘው በቁመቱ በሀገራችን ቀዳሚ በሆነው ግዙፍ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ሥር ሲታዩ የኅብረት እና የጋራ ኃላፊነት ተምሳሌትነቱን ያጎሉታል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
