የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ፍጹም አሰፋ

”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት ቀደም ሲል ሀገራዊ የመረጃ ሥርዓቱ በራስ አቅም ላይ ያልተመሠረተ በውጭ ድጋፍ ጥገኝነት ላይ የቆየና የተዓማኒነት ጥያቄዎች የሚነሱበት እንደነበር አንስተዋል።

‎ከዚህ ለመላቀቅ በተደረጉ ቁርጠኛ እርምጃዎች የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ሪፎርምና የ10 ዓመቱን የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ለመከታተል የሚያስችሉ እንደ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት፣ የቱሪዝም መረጃ እና የቢዝነስ ድርጅቶች ቆጠራ ያሉ የተለያዩ የዳሰሳ ጥናት በማድረግና በዲጂታል ሥርዓት በማዘመን እንዲሁም ለመረጃ ልማት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ የመደመር እሳቤን መሠረት ያደረገ የመረጃ ተኮር ፖሊሲ አመራርና ውሳኔ ሰጪነትን ማረጋገጥ ተችሏል።

‎ይህ ዓይነቱ የሪፎርም ውጤት፤ መረጃዎች በኢትዮጵያ ልጆች እንዲሰበሰቡና እንዲተነተኑ በማድረግ የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የፖሊሲ ነፃነት የሚያረጋግጥ ሲሆን፤ ብሔራዊ ጥቅምን፣ የዜጎችን ደኅንነትና የልማት ትልሞችን በጽኑ መሠረት ላይ በመገንባት ከተለመደው የምላሽ ሰጭነት አሠራር ወደ ቅድመ-ትንበያ መሸጋገር የሚያስችል ዘላቂ ተቋማዊ ዐቅም ፈጥሯል።

#PMOEthiopia#EthiopiaDelivers

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

See less

Similar Posts