የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ ማምጣቱ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር እዮብ ተካልኝ፤ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሀገር ውስጥ መረጋጋትንና ተዓማኒነትን መልሶ ማምጣቱን ገልጸው፤ ይህም የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሪ ገበያውን ነፃ በማድረግ፣ የገንዘብና የፊስካል ፖሊሲን በማዘመን፣ እንዲሁም ለዘላቂና አካታች ዕድገት ጠንካራ መሠረት ለመጣል የፋይናንስ ዘርፉን በማጠናከር የተገኘ መሆኑን አብራርተዋል።


