ሁለተኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ በተግባር!
ለዘመናት የቆየውን የኢኮኖሚ መዛባቶችን እና የመንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ለመቀልበስ በ2011 ዓ.ም. የተጀመረው የመጀመሪያው ምዕራፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ በስንዴ ምርትና በቴሌኮም ዘርፍ ታሪካዊ ስኬቶችን አስመዝግቧል። በእነዚህ ስኬቶች ላይ በመመሥረት የተጀመረው ሁለተኛው ምዕራፍ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ በማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት፣ በንግድ ሥነ ምህዳር፣ እና በዘርፎች ተወዳዳሪነት ላይ በትኩረት እየሠራ ይገኛል። የዚህ ማሻሻያ ቁልፍ ማረጋገጫ በፋይናንስ ዘርፉ ላይ እየታየ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የኢንቨስትመንት ባንኮች በከፍተኛ ፍጥነት ከመስፋፋታቸውም በላይ በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ ሀገር የኢንቨስትመንት ባንክ የሥራ ፈቃድ ተሰጥቷል።
ይህ ታሪካዊ እመርታ ብሔራዊ ትልማችንን ከዓለም አቀፍ ካፒታል ጋር በማገናኘት፣ የውጭ ምንዛሬን ማስገኘትና የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ኢትዮጵያን በገበያ የምትመራ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እያደረጋት ይገኛል።
በማሻሻያው ተጨባጭ እርምጃዎች፣ ሀገራችን ቀጣዩን የኢኮኖሚ ነፃነቷን ምዕራፍ እየጻፈች ነው!


