“የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርትን ይጎብኙ—የ ‘ገበታ ለትውልድ’ ውጥን ፍሬ።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የኢፌዲሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በጋራ በመተባበር የሁለተኛው ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን መሰረታዊ አላማና ግቦችን፤ እንዲሁም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ለሚዲያ ባለሙያዎች ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል። አካባቢን ለመጠበቅ እና ጽዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚዲያ ባለሞያዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ከፍተኛ ሀላፊነት ያለባቸው መሆኑን ገልፀው…
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መከናወን ተከትሎ፤ አዲሱ የመደመር መንግሥት ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. በይፋ ይመሰረታል። ኢትዮጵያ- አዲሲቷ የተስፋ አድማስ #PMOEthiopia#የመደመርመንግሥት ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication Post Views: 108
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባችንን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ ሳይት ጎብኝተናል። በዚህ ሳይት ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፤ የ3ዲ ህትመት(3D printing)፣ የቅድመ-ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ እና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው። እያንዳንዳቸው ግንባታዎች ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ፍጥነት እና ጥራት እርስ በእርስ የማይጋጩ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ጥራታቸውን…
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለመዝጋት መወሰኑን አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ከኤርትራ በኩል ለተሰነዘሩ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ላልሆኑ ጠብ ጫሪ እና የጠላትነት ድርጊቶች የአጸፋ ምላሽ በመስጠት፣ በኤርትራ አስመራ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲውን ለመዝጋት ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል። ሚኒስቴሩ አያይዞም የቪዬና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ስምምነት ድንጋጌዎችን በመጣስ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ቀጥተኛ አደጋ በሚፈጥሩ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት የሚከተለው የጠራና ስትራቴጂካዊ ፖሊሲ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰቱትን ፈታኝ የኢኮኖሚና የነዳጅ ቀውሶች በጽናት እንድትመክት የሚያስችል ጠንካራ ሉዓላዊ አቅም አጎናጽፏታል። ይህ ሀገራዊ የጽናት ልዕልና በተጨባጭ የታየው እንደ ሊፍታንዛ ያሉ ግዙፍ የአውሮፓ አየር መንገዶች በነዳጅ እጥረት አቅም አንሷቸው በረራ እስከመቀነስና ሌሎች ሀገራት ደግሞ በአጭር ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ በረራ ለማቋረጥ…
129ኛው የዓድዋ ድል በዓል በድምቀት ተከበረ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ታሪካዊዉ የዘንድሮ የዓድዋ ድል በዓል፣ “ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል” በሚል መሪ ቃል የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሐመድ እና የቀድሞው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማትን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፤ አርበኞች፣ የመከላከያና የፀጥታ አካላት አመራሮች፣ ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች…