የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሀገሪቱን ከጥገኝነትና አጀንዳ ተቀባይነት በማላቀቅ ታሪኳን፣ ነፃነቷንና እያደገች ያለችበትን ፍጥነት የሚመጥን ተፅዕኖ ፈጣሪነት አጎናፅፏታል።

ይህ ማዕቀፍ በአራቱ ዓበይት መርሆዎች ተቃኝቶ የሚመራ ሲሆን፣ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረኮች ንቁ (Active) ተሳታፊ፣ ከአንድ የፖለቲካ ጎራ ብቻ ሳትወሰን አማራጭ (Alternative) ዲፕሎማሲን የምትከተል፣ ፈጣን የጂኦፖለቲካ ለውጦችን በጥበብ በመከታተል ከሁኔታዎች ጋር ተላማጅ (Adaptive) እና የሌሎችን ፍላጎት ከመቀበል ይልቅ ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስከብር አጀንዳ ቀራጭ (Agenda Setter) በመሆን ስትራቴጂካዊ ራስን የመቻል መንገድ እንድትቀይስ አድርጓታል። ሀገሪቱ ይህንን የዲፕሎማሲ ቁመና ለማስጠበቅ የሚስያስችላትን የኢኮኖሚ፣ የመከላከያ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ እና የቴክኖሎጂ አቅሟን በጽኑ መሰረት ላይ በፍጥነት እየገነባች ትገኛለች።

Similar Posts