የገጠር ልማት መለካት ያለበት በሚገነቡት መሠረተ ልማቶች ብቻ ሳይሆን፣ ተከትሎ በሚመጣው የሰዎች ሕይወት ለውጥ መሆን አለበት።

‎‎በመሆኑም የገጠር ኮሪደር ልማት ውጥን ተግባራዊና ሰውን ማዕከል ያደረገ አካሄድን በመከተል ላይ ይገኛል። ይህም ትስስርን ማሻሻል፣ ምቹ የኑሮ ሁኔታዎችን መፍጠር እና በገጠር ማሕበረሰብ ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋፋት ነው።

‎‎የዚህ ዐበይት ግብ የተበታተነና የተቆራረጠ ሐብትን በማስተካከል አምራች፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ፣ ዘላቂ ልማት ያላቸው እንዲሁም ለመኖርና ለመሥራት ማራኪ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን መገንባት ነው።

#PMOEthiopia#EthiopiaDelivers

Similar Posts