«ተስፋን እንትከል»

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር አብሮ በመሆን «ተስፋን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረውን የዚህን ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያን በጋራ የችግኝ ተከላ በማካሄድ አከናውነዋል።

‎የ2018 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መጠናቀቅን ስናበስር የተተከለው እያንዳንዱ ችግኝ የሕብረታችን፣ የሕዳሴያችንና የዘላቂ እድገታችን ሕያው ምልክት መሆኑን በማስታወስ ነው።‎

‎በጽኑ አንድነታችንና በጋራ ጥረታችን የታነጸች፣ የበለጸገችና ብሩህ ኢትዮጵያን ለማየት ሙሉ ተስፋ ሰንቀን ወደፊት እንገሰግሳለን!

Similar Posts