ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትን ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ኬንያ ገብተዋል።


የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚሟላው ከንጹህ የኃይል አቅርቦት ላይ ነው። ይህም በዓለማችን ካሉ ጥቂት ሀገራት ተርታ ያሰልፈናል። #PMOEthiopia Post Views: 45
ዛሬ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ትዕይንቶች ተደርገዋል። ሕዝቡ በዚህ ትዕይንተ ሕዝብ ላይ ለሰላም ያለውን አቋም በድጋሚ ገልጿል። ፀረ ሰላምና ተላላኪ ኃይሎች በሚፈጽሙበት ግፍ ተማሯል። በደሙና በላቡ የገነባቸው መሠረተ ልማቶች ‘የአንተ ነን’ በሚሉት የጠላት ተላላኪዎች ሲፈርሱበት በአይኑ አይቷል። ልጆቹ ከትምህርት፣ ከብቶቹ ከግጦሽ እየተከለከሉ እጅ ከወርች ታስሮ ከርሟል። በዚህ የተነሣ ተላላኪዎቹን ጽንፈኞች ለመታገል ቆርጦ የተነሳው ሕዝብ…
“የላፍቶ ሆስፒታል ተመረቀ! በኢትዮጵያ በተሻሻለው የመከላከል እና አክሞ የማዳን የጤና ፖሊሲ መሠርት ፣ ሀገራችንን ቀዳሚ የህክምና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ፣ ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ ለሰነቅነው ርዕይ እና መሰል የረቀቁ የዘርፉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንባታን ለማስቀጠል የላፍቶ ሆስፒታል አሻጋሪ ምዕራፍ ነው። በ5.4 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ዘመናዊና ግዙፉ የላፍቶ ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ…
መጪዉን የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በዓልን አስመልክቶ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሠራተኞች የበዓል ስጦታዎችን አበርክተዋል:: እንዲሁም በጸ/ቤቱ ድጋፍ ለሚያድጉ ሕፃናት የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ አበርክተዋል። Post Views: 31
“በያቤሎ ከተማ የሚገኘው የቦረና ባሕል ማዕከል ዛሬ ተመርቋል። በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ2013 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ ተቀምጦለት የነበረውና ዛሬ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የባህል ማዕከል፤ በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የተገነባ ሲሆን በ57.6 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። ማዕከሉ የገዳን ሥርዓት ለማሳየት በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረገ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 2000 ሰዎች ማስተናገድ አቅም ያለው የስብሰባ አዳራሽ እና…
Post Views: 75