በጂኦግራፊ የተሳሰሩ ጎረቤታሞች፤ በውይይት መግባባትንና ወዳጅነትን የሚያጸኑ አጋሮች::




ባለፉት የሪፎርም ዓመታት ሕገ መንግሥታዊነትን ለማረጋገጥ፣ የመብቶችን ጥበቃ ለማስፋትና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የሚያስችሉ ሰፋፊ የሕግና ተቋማዊ ማሻሻያዎች የተደረጉ ሲሆን በዚህ ሒደት ከተለዩት ቁልፍ ሕጎች መካከል አንዱ የወንጀል ሥነ ሥርዓት የሕግ መድብሉ ነው። የ1954 የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት እና ከወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ…
በመጪዉ ዓመት የሚኖሩ ፈታናዎችን አስቀድሞ በመገንዘብና የመሻገሪያ መንገዶችን ለመተለም ዜጎች ምንጊዜም ንቁ መሆን አለባቸዉ ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ የዘንድሮ የጷጉሜን ቀናት ስያሜን ተንተርሶ በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም የተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት ሀገሪቱ ዉስብስብ ችግሮችን በመሻገር በሁሉም ዘርፎች አኩሪና እምርታዊ ድሎች ያስመዘገበችበት ዓመት እንደ ነበር አስታዉሰዋል፡፡…
“በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል። በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ…
“ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች! በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል። ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም…
ጳጉሜን 1 ቀን 2016 ዓ/ም በዛሬው ዕለት በመላው የሀገሪቱ አካባቢዎች “የመሻገር ቀን” በሚል ስያሜ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል፡፡ ዕለቱ “የመሻገር ጥሪቶች፣ የአዲስ ብርሃን ወረቶች በሚል መሪ ቃል” ይከበራል፡፡ መሻገር ከአንዱ ወደ ሌላኛው የሕይወት ምዕራፍ ሽግግር የምናደርግበት ተፈጥሯዊ ሂደት ነው። አሮጌዉ ዘመን ተጠናቅቆ ወደ ዐዲሱ ዓመት የምንሸጋገርባት የጳጕሜን ወር የመጀመሪያው ዕለትን ስናከበር በተጠናቀቀዉ ዓመት ስኬቶችን ያስመዘገብንባቸው…