የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።

‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።”

Similar Posts