Similar Posts
ሰላም እንዲመጣ መንግሥት ምን አደረገ ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) Post Views: 49
ዛሬ ማለዳ በባሌ ዞን፣ ደሎ መና ወረዳ በመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አማካኝነት የተጀመረውን የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀናል። ፕሮጀክቱ የወልመል ወንዝን በመስኖ በሚገባ በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን በማላቅ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወነ ነው። ፕሮጀክቱ ዘላቂ የገጸምድር የመስኖ ሥርዓት በመገንባት የግብርና ስራው ለዘመናት በዝናብ ውሃ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የአካባቢውን ሕዝብ ዘላቂ የኑሮ ዘዴ ለማጎናፀፍ ታልሞ ተከናውኗል።
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት 20,000 ለሚሆኑ አርሶአደሮች ለሚያገለግል 9687.45 ሄክታር የእርሻ መሬት አስተማማኝ የመስኖ አቅርቦት ይኖረዋል። ይኽም የግብርና ምርታማነትን የሚያሳደግ፣ ለድርቅ የማይበገር ከባቢን የሚፈጥር ብሎም በማኅበረሰቡ አዳዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ከነዚህ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ባሻገር የአካባቢውን የውሃ አስተዳደር ተቋማትን በማጠናከር፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባለቤትነት በማሳደግ ብሎም የወልወልን ወንዝ ዘላቂ አጠቃቀም በማጎልበት የተሻለ የምግብ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሰውን የፋሲል ጊቢ መርቀዋል።
የተከናወነው ሰፊ የእድሳት ሥራ በቅርስ ስፍራው ነባሩን ታሪክ በመጠበቅ ውበቱን እና ተደራሽነቱን በማሻሻል አዲስ እስትንፋስ የሰጠ ሆኗል። የእድሳት ሥራው የቤተመንግሥቱን የግንባታ መዋቅር መጠገን፣ የእግር መንገዶችን ማሻሻል፣ ቁልፍ የሆኑ ሕንፃዎችን ከዝግባ እና ዋንዛ በባሕላዊ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ በማደስ የስፍራውን ግለ ወጥ መልክ እና ባሕርይ ለመጠበቅ ተሰርቷል። ለጎብኝዎች ምቾት የተሰናዱ አገልግሎት መስጫዎችም ትርጉም ባለው ደረጃ ተሻሽለዋል። አዲስ የቱሪስት…
“ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት እና ከኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ አጄይ ባንጋ ጋር መወያየት ሁልጊዜም ቢሆን አስደሳች ነው። በመካሄድ ላይ ስላሉት በአለም ባንክ ቡድን ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተናል። ይኸውም በጤና፣ በኃይል ምንጭ እና የአየር ንብረት ጥበቃ የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ጉዳይን የተመለከተ ነበር። Always a great pleasure meeting with Ajay Banga, President of the World Bank and…
“ጉልበት ይሸሻል፣ ጊዜ ይሸሻል፣ ስልጣን ይሸሻል፣ ሁሉ አላፊ ነው ፣ የማያልፈው እንደዚህ ያለው ታላቅ ስራ ነው።”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) Post Views: 84
ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር በቀጠናዊ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር፣ እና በሁለትዮሽ ግንኙነት በትምህርት ፣ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ እና በኢትዮጵያ በተከፈተው የኢኮኖሚ ምኅዳር ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ተወያይተናል። ውይይታችን የሁለትዮሽ ትስስራችንን እና የጋራ ጥቅም ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ያለንን አቋም ያጠናከረም ነበር። Met with President Alexander Stubb of Finland for bilateral discussions on regional issues, multilateral cooperation,…
