Similar Posts
የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ንረትን ለመቀነስ መንግሥት ምን አደረገ ?
“የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ፈተና ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በአንዳንድ ሀገራት ከ400 ፐርሰንት በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ ነው፡፡ ከአፍሪካም 172 ፐርሰንት የደረሰ የዋጋ ንረት ያጋጠመ ሲሆን በጎረቤት ሀገራት እንኳን 72 ፐርሰንት የደረሰ የዋጋ ግሽበት ተመዝግቧል ። ከለውጡ ወዲህ መንግሥት አለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ቀድሞ በመገምገም ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የኑሮ ውድነት ጫናን በዘላቂነት ለመቀነስ በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ…
“ከአለም ባንክ ፕሬዝደንት እና ከኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ አጄይ ባንጋ ጋር መወያየት ሁልጊዜም ቢሆን አስደሳች ነው። በመካሄድ ላይ ስላሉት በአለም ባንክ ቡድን ለኢትዮጵያ የሚደረጉ ድጋፎች ዙሪያ ተወያይተናል። ይኸውም በጤና፣ በኃይል ምንጭ እና የአየር ንብረት ጥበቃ የልማት ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ጉዳይን የተመለከተ ነበር። Always a great pleasure meeting with Ajay Banga, President of the World Bank and…
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ! ዘንድሮ የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የምናከብረው የተነገረው የተስፋ ቃል መድረሱን፣ የለውጥ ብርሃን መፈንጠቅ መጀመሩን፣ የመሻገር ዘመን መቅረቡን እያመንን ነው። ጉዟችን በውጣ ውረድ የተሞላ ነበር፤ ተስፋ አስቆራጭ መከራዎችን አስተናግደናል። ከእንግዲህ ፈተናው ጨርሶ አይጎበኘንም ባንልም፣ ተስፋችን የሚወለድበት የዋዜማው ዕለት ላይ ደርሰናል። የፍዳው ዘመን ላይመለስ ተሸኝቶ፣ የማንሠራራት ዘመን እንደመጣ በልበ ሙሉነት መናገር እንችላለን።…
መላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አለን!
ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አለን! በአንድ ጀንበር 567 ሚሊየን ችግኝ ተክለናል! በታሪካዊ ቀን ታሪክ የማይረሳውን ስኬት አስመዝግበናል! አሳክተነዋል! #GreenLegacy Post Views: 626
በኃብት ስጦታ አንፃር ስንመለከት ኢትዮጵያ ለሁሉም የሚበቃ ኃብት እንዳላት እናውቃለን። በባሌ ዞን ከተለያዩ አመራሮች ጋር ያደረግነው ጉብኝት የመጨረሻ መዳረሻ አስደማሚው የፊንጫ ሀበራ ፏፏቴ ሆኗል። በግርማ የሚወርደው ፏፏቴ ወደ ሶፍኡመር የዋሻ ሥርዓት የሚደመረውን የወይብ ወንዝ የሚቀላቀል ነው። የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ የሚገኝበት ይኽ አስደናቂ ከባቢ ድንቅ የአዕዋፍ መገኛና በቅርቡ የዋሻ መስህብ የተገኘበት እንዲሁም የራፉ ውብ የዐለት ደን አቅራብያ የሚገኝ ነው። በቅርቡ በአካባቢው የሚገነባው ማረፊያ ሲጠናቀቅም ለጎብኝዎች የበለጠ ሳቢ እና ምቹ ይሆናል።
ባለፉት ሶስት ቀናት በጉብኝቱ የተሳተፉ የቀድሞ እና በሥራ ላይ ያሉ ኃላፊዎች በጉብኝቱ የተመለከቱት የተፈጥሮ፣ የባሕል እና የሰው ኃብት ከፍ ያለ መነሳሳትን ፈጥሮላቸዋል። የጋራ ሥራችን እነዚህን ኃብቶቻችንን መግለጥ፣ ማሳደግ፣ በኃብቶቹ ላይ በመጨመር ቀጣዩ ትውልድ ችቦውን ተረክቦ እንዲቀጥል መሠረት መጣል ነው። ኢትዮጵያ በርግጥም የተትረፈረፈ ኃብት ምድር ናት። እንሰባሰብ። ለማለም እንድፈር። የጋራ ነጋችንን በጋራ እንገንባ። Gama qabeenyaatiin yoo…
ዛሬ ማለዳ በባሌ ዞን፣ ደሎ መና ወረዳ በመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አማካኝነት የተጀመረውን የወልመል ወንዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀናል። ፕሮጀክቱ የወልመል ወንዝን በመስኖ በሚገባ በመጠቀም የግብርና ምርታማነትን በማላቅ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተከናወነ ነው። ፕሮጀክቱ ዘላቂ የገጸምድር የመስኖ ሥርዓት በመገንባት የግብርና ስራው ለዘመናት በዝናብ ውሃ ላይ ተመስርቶ የነበረውን የአካባቢውን ሕዝብ ዘላቂ የኑሮ ዘዴ ለማጎናፀፍ ታልሞ ተከናውኗል።
ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ተግባር በሚገባበት ወቅት 20,000 ለሚሆኑ አርሶአደሮች ለሚያገለግል 9687.45 ሄክታር የእርሻ መሬት አስተማማኝ የመስኖ አቅርቦት ይኖረዋል። ይኽም የግብርና ምርታማነትን የሚያሳደግ፣ ለድርቅ የማይበገር ከባቢን የሚፈጥር ብሎም በማኅበረሰቡ አዳዲስ የሥራ እድል የሚፈጥር ይሆናል። ከነዚህ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች ባሻገር የአካባቢውን የውሃ አስተዳደር ተቋማትን በማጠናከር፣ የአካባቢውን ሕዝብ ባለቤትነት በማሳደግ ብሎም የወልወልን ወንዝ ዘላቂ አጠቃቀም በማጎልበት የተሻለ የምግብ…
