የሰርቪስ ሴክተር አፈጻጸምን በተመለከተ፣

• የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመት 8 ሚሊዮን ሰዉ ሲያጓጓዝ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት 6 ወራት 10.7 ሚሊዮን ሰዉ አጓጉዟል፡፡ በዚህ ዓመት በትንሹ ወደ 22 ሚሊዮን ለማድረስ እየተሰራ ነዉ፡፡ አየር መንገዱ በመጠን፣ በመዳረሻና በሚያጓጉዘዉ ሰዉ በእጅጉ ጨምሯል፡፡

• ሞባይልን በተመለከተ በለዉጡ ጊዜ 37 ሚሊዮን ዜጎች ሞባይልን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ዘሬ ኢትዮ-ቴሌኮም ብቻ 87 ሚሊዮን ዜጎች፣ ሳፋሪኮም ደግሞ ከ10 ሚሊዮን ዜጎች በድምሩ ከ97 ሚሊዮን ሰዉ በላይ ሞባይል ይጠቀማል፡፡ ይህ 60 ሚሊዮን ጭማሪ ያለዉ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህ ትልቅ ዉጤት ነዉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር

#የጠሚሩምላሾች

Similar Posts