ምስጋና ይገባቸዋል

“የምትተክል ሃገር የሚያጸና ትውልድ” የ600 ሚሊዮን ችግኞች የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከማለዳው12 ሰአት ጀምሮ እስከ አመሻሽ 12 ሰዓት በመላ ሃገሪቱ ሲካሄድ ለኢትዮጵያዊያንና ለመላው ዓለም መረጃውን ለማድረስ በከፍተኛ ትጋት ኃላፊነታችሁን ለተወጣችሁ የመገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ላቅ ያለ ምሥጋናውን ያቀርባል፡፡
ሰላማዊት ካሳ
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ
በዚህ ለአንድ ቀን በተካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመላ ሃገሪቱ ከ2 ሺህ በላይ የሚዲያ ባለሙያዎች በተለያዩ የሃገር ውስጥና የውጭ ቋንቋዎች መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ሲያቀርቡ ዉለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በፌዴራልና በክልል የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሥራውን በማስተባበር እና ለሚዲያ ባለሙያዎች ተገቢውን እገዛ በማድረግ ላደረጉት ጥረት ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡