ብቃትና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲቻል በርካታ የሪፎርም ሥራዎች እየተሰሩ ነው

|

ዶክተር ለገሰ ቱሉ

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር

የሲቪሽ ሰርቪስ አገልግሎቱ ከማንኛውም ኃላ ቀር አሰራርና አመለካከቶች ተላቆ ዘመኑ የሚፈልገውን ብታቅና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል በርካታ የሪፎርም ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ተናገሩ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች “አገልጋይና ስልጡን ሲቪስ ሰርቪስ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ በሚል ርዕስ በተካሄደ ውይይት ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት ሲቪል ሰርቪሱ የሚጠበቅበትን ጥራት ያለው ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት እንዲሰጥ ይጠበቃል፡፡

ይህንን ዕውን ለማድረግ ከአሁን ቀደም ያልተነበረ የሲቪስ ሰርቪስ ፖሊሲ ከመቅረጽ ጀምሮ፣የተለያዩ አዋጆች እየተዘጋጁ መሆኑንና አዋጆቹንም ተከትሎ ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችሉ መመሪያዎች በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡፡

ሲቪስ ሰርቪሱ ከዚህ ባሻገር ኢትዮጵያን መምሰል እንደሚጠበቅበት ዶክተር ለገሰ አንስተው ብቃትን መሰረት ያደረገ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ማስተናገድ የሚችል አካታች ሲቪስ ሰርቪስ መገንባት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ዘመናት ለምን ጠንካራና ስልጡን ሲቪስ ሰርቪስ መገንባት አልቻልንም የሚለውን ጥያቄ ሁላችንም ልንመልስ ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ ሲቪስ ሰርቪሱ ከፖለቲካ አመለካከት፣የሀይማት፣ከዘርና መሰል ጉዳዮች ነጻ ሊሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ሲቪስ ሰርቪሱ የመንግስትን ሕጎች፣ደንቦችና መመሪያዎች የመፈጸም ግዴታ ነው ያለበት ያሉት ዶክተር ለገሰ ከዚህ ውጪ ለአንድ ወገን ያደላ፣አንዱን አቅርቦ ሌላውን የሚያገል አሰራር በሲቪስ ሰርቪሱ ውስጥ አይፈቀድም ብለዋል፡፡

በቀጣይ ዘመኑ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ የሲቪስ ሰርቪስ አገልግሎት ለመስጠት ሠራተኞች ራሳቸውን ከዘመኑ ጋር በማዘመን ወቅቱ የሚጠይቀውን አሰራርና አመለካከት በመላበስ ሊያዘጋጁ እንደሚገባን አንስተዋል፡፡

Similar Posts