አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ነዉ _ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
(ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም) አረንጓዴ አሻራ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራርና አጠቃላይ ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር ዘነበወርቅ የሚገኘዉ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጧል፡፡
በኢቢሲ ግቢ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በርካታ የቡና ችግኞች ተተክለዋል፡፡
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክቡር ለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተልዕኮ አካል የሆነውን ኢትዮጵያን የማንሰራራት ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ መረሐ ግብሩ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል፡
የአረንጓዴ አሻራ እንደ ሀገር ከተጀመረ አንስቶ ተቋሙ መረጃዎችን ተደራሽ ከማድረግ ባሻገር በአረንጓዴ አሻራ መረሐ ግብር ላይ በንቃት መሳተፉን ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት የተደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም የተቋሙ ሀገራዊ እና ማህበራዊ ኃላፊነት አካል መሆናቸውን ጠቁመዋል። ሌሎችም እንድትክሉ በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ አቶ ከበዴ ዴሲሳ በበኩላቸው መርሐ ግብሩ ችግኝን ከመትከል በላይ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ተነግረዋል።
በቀጣይም የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች የአረንጓዴ አሻራን ከማኖር ባሻገር ቀጣይነትም ያለው እንክብካቤ የማድረግ ስራን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡




