ኢትዮጵያና ድል!
ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውንም ሀገር በመውረር አትታወቅም። ወደፊትም ያ ፍላጎት የላትም። ሌሎች ማወቅ ያለባችው ግን ትንሽም ይሁን ትልቅ። ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም። ይሄ በጂኦግራፊ የታጠረ ጉዳይ አይደለም። ማንም ነው ያልኩት። አድዋ ይደገማል፤ አትሞክሩን!

ኢትዮጵያ በታሪኳ የትኛውንም ሀገር በመውረር አትታወቅም። ወደፊትም ያ ፍላጎት የላትም። ሌሎች ማወቅ ያለባችው ግን ትንሽም ይሁን ትልቅ። ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም። ይሄ በጂኦግራፊ የታጠረ ጉዳይ አይደለም። ማንም ነው ያልኩት። አድዋ ይደገማል፤ አትሞክሩን!

የኢኮኖሚ መልሶ ክለሳን በተመለከተ ባለፉት አስራ አንድ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ክለሳ ተካሄዶ አያውቅም። በመሆኑም አዳዲስ የተጨመሩ ኢኮኖሚዎችን ለማካተትና ሚና የሌላቸውን የኢኮኖሚ ዘርፎችን ለማስወጣት ባለፉት አንድ ዓመታት ከፍተኛ የሰው ኃይል በማሰማራት የኢኮኖሚ ክለሳ ሲካሄድ ቆይቷል። ከዚህ በፊት በኢኮኖሚ ያልተካተቱ ዲጂታል ኢኮኖሚ፣ የኮሪደር ልማት፣ ክላስተር ግብርና፣ ሌማት ትሩፋት፣ ተጨማሪ ኢንዱስሪ ፓርክ ፣ አረንጓዴ አሻራ፣ አዳዲስ የኢነርጂ ፕሮጀክቶች…
ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቀችው በፈተናዎች ወስጥ አልፋ ነው። ኢትዮጵያ በተደራጁ ሰራዊቶቿ፤ የተባበረ ልብ ባላቸው ህዝቦቿ እንዲሁም ዋጋ ለመክፈል በማይሰሰቱ ልጆቿ አማካኝነት ፈተናዎችን ተሻግራ ስሟን አጽንታ ይዛለች። Post Views: 16
ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ብዝኃ ማንነት ደምቃ፣ ፀንታና ታፍራ የኖረች፣ ብዝኃ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት የሆነች ድንቅ ሀገር ናት፡፡ ብዝኃነታችን የጥንካሬያችን፣ የሥልጣኔያችን፣ የአይበገሬነታችን፣ የክብራችን፣ የነፃነታችን እና የአልሸነፍ ባይነታችን ምሥጢር ነው፡፡ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ ጥንታዊ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቦታዎች እና የኪነ ሕንጻ ሀብቶቻችን የብዝኃነታችን ውጤቶች ናቸው፡፡ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የለጋ ኦዳ ዋሻ…
በንግግር በሠላማዊ መንገድ ችግሮችን መፍታት የስልጣኔ ምልክት ነው። ታጋሽነት፣ ቻይነትና ይቅር ባይነትን መላበስ ለሀገር ግንባታ በእጅጉን ያግዛል። ሠላምን የምናስቀድመው የአንድ ቀን እረፍት ለእናቶች ያለውን ጥቅም ስለምናውቅ ነው። ስለ ሀገር የሚከፈል ዋጋ መረር ያለ እውነትን መቀበል ይፈልጋል፤ ከዛ ውስጥ አንዱ ይቅርታ ነው። ይቅርታን የምናስቀድመውም ንግግርና ሰላም ለኢትዮጵያም ለቀጣናውም እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ ነው። Post Views: 15
Post Views: 255
********************************** ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት እመርታዊ ስኬቶችን እያስመዘገበች የሚመጥናትን ከፍታ እየያዘች ትገኛለች። ለዘመናት የቁጭት እና እንጉርጉሮ ትርክት ምንጭ የነበረዉን ዓባይን ገርታ የኃይል እና ብርሃን ምንጭ አድርጋለች፡፡ በንጋት ኃይቅ በምግብ ሉዓላዊነቷ ላይ ጉልህ ሚና የሚጫወት የዓሣ ምርት ማግኘት ችላለች፤ ዐዲስ የቱሪዝም መዳረሻ ደሴቶችንና ከተሞችን ፈጥራለች፡፡ የዓባይን የቁጭት ትርክት ወደ ድል እና አሸናፊነት ብስራት ቀይራለች፡፡ ተጨማሪ…