የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የባህር በር አስፈላጊነትን በተመለከተ !!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የአምራች ኢንዱስትሪው የታለመለትን ብሔራዊ ግብ እንዲመታ አስተማማኝ የሎጂስቲክስ መዋቅርና የባህር በር አማራጮች መኖራቸው አማራጭ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ ነው። ምርቶችን በብዛትና በጥራት ማምረት በራሱ በቂ አይደለም ዋናው ቁምነገር ያመረቱትን ውጤት በብቃት፣ በቅልጥፍና እና በተወዳዳሪነት ለዓለም አቀፍ ገበያ ማድረስ መቻል ነው።ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ የራሷ የሆነ ወይም በውል የተረጋገጠ የባህር በር የማግኘት ጥያቄ ቅንጦት ሳይሆን የሀገሪቱ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በውል መገንዘብ ያስፈልጋል ። ይህ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ከማንኛውም አካል ጋር ግጭት ለመፍጠር የታለመ ሳይሆን የ130 ሚሊዮን ሕዝብን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በፅኑ መሠረት ላይ ለማቆም እንዲሁም የሀገሪቱን የኢንዱስትሪ ውጤቶች ያለምንም ስጋትና እንግልት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ያለመ ነው ።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts