የዲሞክራሲ ልምምድ የመቅረጽ፣ የመግራት፣ የማስፋት እና የማጽናት ሚና የሚዲያው የቤት ሥራ !
ግንቦት 14 /2018 ዓ.ም
7ተኛውን ሀገራዊ ምርጫን ሀገርን በጽኑ መሠረት ላይ የምንገነባበት እና ስንደመር ምን ያህል ታላቅ ነገር ማድረግ እንደምንችል ለዓለም በተግባር የምናሳይበት የታሪክ አጋጣሚ ማድረግ ይገባል።
ጀግኖች ከአደዋ ዜሮ ዜሮ ተነስተው በአንድነት ጸንተው ሀገርን እንዳስረከቡን የሚዲያው ዘረፍም ለኢትዮጵያ ከፍታ በቃል ኪዳን አስሮ ከዚሁ ሥፍራ ስለሀገር በአንድነት ተነስቷል ።
የዴሞክራሲ ግንባታ የሀገረ መንግሥት ማጽኛ አንዱ ምሶሶ መሆኑ በተመከረበት በዚህ መድረክ የዲሞክራሲ ልምምድ የመቅረጽ የመግራት የማስፋት እና የማጽናት ሚና የሚዲያው የቤት ሥራ መሆኑ በሚዲያ ቤተሰቡ ተሰምሮበታል ።
ከ25 በላይ የሆኑ የኢትዮጵያ ሚዲያዎች በአንድነት በሞከሩበት በዚህ የውይይት መድረክ ሚዲያዎች በሀገር ብሔራዊ ጥቅሞች ላይ እንዴት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ሰፊ ውይይት በማድረግ 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫን ለማሳካት የግብአት እና የሰው ሀይልን በማቀናጀት በጋራ ለመስራት ውል አስረውበታል ።
የኢፌድሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት










