የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

“በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ በአንታሊያ ቱርክ በመገኘት ከቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

‎‎በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት መሠረት በማድረግ፣ የሁለትዮሽ ትብብራችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተወያይተናል።

‎‎COP31ን ለማስተናገድ ለተደረገው ዝግጅት እና ጉባኤው በድምቀትና በስኬት እንዲጠናቀቅ ቱርክዬ እያሳየችው ላለው ጥረት አድናቆቴን ገልጫለሁ። ይህም ኢትዮጵያ የCOP32 ፕሬዝዳንትነትን ለመረከብ በምታደርገው ዝግጅት ላይ የሚኖረውን አጋርነት እንዲሁም የጋራ ትኩረት በሚሹ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመተባበር የሚያስችሉ ዕድሎችን ተመልክተናል።”

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts