የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ የተከበሩ ካያ ካላስን ዛሬ ተቀብዬ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።
በአውሮፓ ሕብረት እና በአፍሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር ላይ የመከርን ሲሆን በጋራ ጥቅሞች እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሃሳብ ተለዋውጠናል።
በተጨማሪም ትኩረት የሚሹና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መሰረት ባደረገው ውይይታችን፤ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ይበልጥ ለማሳደግና ለማስፋፋት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ መክረናል።”
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication



