የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
“የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነሥርዓት፤ የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ፣ መጠነ ሰፊ እድሎችን ለመፍጠር እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ለላቀ ኢኮኖሚያዊና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነትን መሰረት ለመጣል ትልቅ እርምጃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሁነት ነው።
በአህጉራችን የምትገኙ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ስራ ፈጣሪዎች፤ በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት ልታደርጉ፣ ባለን አቅምና የጋራ ጸጋ እምነት ሊኖራችሁ እንዲሁም አህጉራዊ መፃኢ እድላችንን የሚወስኑ ለውጥ አምጪ ፕሮጀክቶችን ልትገነቡ ይገባል።
የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው!”





