የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ዓበይት ስኬቶችን ባቀረቡት ሪፖርት፦
ዘርፉ ከለውጡ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በመለየት ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ስኬቶች መካከል፤ ለ30 ዓመታት የቆየው የጤና ፓሊሲን በመከለስ፣ መከላከል ከሚለው መርህ በተጨማሪ አክሞ የማዳን ቁርጠኛ የፖሊሲ አመራር፣ የተቋም ግንባታ፣ የጤና መሠረተ ልማት ለውጦች፣ መድሃኒት፣ ክትባት እና የህክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት እና ቁጥጥር ጭማሪ እንዲሁም የጤና ፋይናንስ እመርታ ቁልፍ እና ዋነኞቹ የለውጥ ስራዎች ናቸው።
በተለይም የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃትና ቁጥራቸውን ማሳደግ፤ የዲጂታል ጤና፣ በዘርፉ የተተገበሩ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ ያስመዘገበቻቸው ግንባር ቀደም ስኬቶቿ ናቸው።
የጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ከፍ ያሉ እመርታዎች የተመዘገበበት አንዱና ዋነኛው መስክ ሲሆን ኢትዮጵያ በተለያዩ መድረኮች ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ድርድሮችን እና ንግግሮችን እንድትመራ አስችሏታል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

