የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ በስራና ክህሎት ዘርፍ በለውጡ ዓመታት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችውን ስኬቶች አብራርተዋል።

ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ትኩረት በማድረግና ብቁ የሰው ሀብት እንዲሁም ምቹ እና አስተማማኝ የሥራ ዕድል የተፈጠረባት ኢትዮጵያን ማየት የተለመው ይህ ዘርፍ፤ ከለውጡ በኋላ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የስራ ስመሪት እንዲሁም ዜጎች በቤት ውስጥ እና ባሉበት ሆነው በሚሰሯቸው ስራዎች አማካኝነት ለ19,872,846 ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል።

ይህን ታላቅ ስኬት ለማስመዝገብ ያስቻለው፤ ኢንተርፕርነር ተቋማትን በመፍጠር፣ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ተቋማት ጋር አጋርነት በመፍጠር፣ የቢዝነስ መስፋፋት እና የልህቀት ማዕከላት በማሳደግ፣ ቲቬት ዲጂታላይዜሽን በማረጋገጥ ሰፊ ስራዎች በመተግበራቸው የተገኘ ውጤት ነው።

#PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

https://linktr.ee/FDREGovermentCommunication

Similar Posts