ገራችን ኢትዮጵያ ወደ ላቀ እድገት ጉዞ እየተሸጋገረች ነው – የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት

ኢትዮጵያ በለውጡ መንግሥት በርካታ ችግሮችን በመርታት እና ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማፋጠን ወደ ላቀ እድገት ምዕራፍ እየተሸጋገረች መሆኗን የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ገለጹ።

ከዘመናት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ብዥታ ወጥታ አሁን የጠራ የእድገት ጉዞ ይዛ ወደ ፊት መራመድ በመጀመሯ የተደበቀ እምቅ አቅሟ ይበልጥ የተገለጠ፣ ቶሎ የማደግ ተስፋችንም እየለመለመና ደረጃ በደረጃ እየተጨበጠ መምጣቱን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በእውቀት፣ በጉልበትና በገንዘብ የላብና የእንባ ውጤት የሆነውን ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ከተባበርንና በአንድነት ለሀገር ጥቅም ከሰራን ምንም የሚሳነን ነገር እንደሌለ ያረጋገጠ ታሪካዊ ክንውን መሆኑንም ጠቅሰዋል።

እነዚህና መሰል ድሎችን ለማስቀጠል የተጀማመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቁ ተስፋ አለን ያሉት የምክር ቤት አባላቱ፣ መንግሥት ተስፋ ሰጪ የሆኑ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ለውጦችን በላቀ ቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባም አስገንዘበዋል።

Similar Posts