ጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አሕመድአራተኛውን “የመደመር መንግስት” የተሰኘዉን መጽሐፍ አስመረቁ
መስከረም 6/2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አራተኛውን “የመደመር መንግስት” የተሰኘዉን መጽሐፍ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬክሽን ማዕከል በትላንትናው ዕለት በይፋ አስመርቀዋል፡፡
አድሱ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ብልጽግና ጉዞ ዉስጥ የተገኙ ሁሉ አቀፍ ዉጤቶችና ተግዳሮቶች፣ እድሎችና ስጋቶች፣ እንዲሁም ተጨባጭ መፍትሔዎችን በማቅረብ የመደመር ፍልስፍናን በጥልቀት የሚተነትን ነዉ፡፡
በተለይም መጽሐፉ በዲጂታል ኢትዮጵያ የታገዘ ቀልጣፋ የህዝብ አስተዳደር ገጽታ፣ ሀገራዊ አንድነት እና ሁሉ አቀፍ የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ አዳዲስ፣ ስልጡን እና ሳይንሳዊ ሀሳቦችን ያካተተ ነው፡፡
አዲሱ መጽሐፍ የመድመር ፍልስፍና አካል ሲሆን በህዝቡ በተለይም በወጣቱ ትዉልድ መካከል የትብብር ለውጥ እና የመተሳሰብ እሴት እንዲጎለብት በማድረግ ሀገራዊ አንድነትን ይበልጥ የሚያጠናክር ነዉ፡፡
በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የስራ ሀላፊዎች፣ ምሁራን፣ የሚዲያ ተወካዮች፣ ታዋቂ አክቲቪስቶች እና ዲፕሎማቶች የተገኙ ሲሆን፣ ይህም በሀገሪቱ ፖለቲካዊ ምህዳር ከማጠናከር አንጻር ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእስካሁኑ የህትመት አበርክቶ ኢኮኖሚያዊ የፖለቲካ ሽግግር እና በሀገር ግንባታ ሂደት ዉስጥ፣ እንዲሁም የህዝብ ተሳትፎን ቀጣይነት እንዲኖረዉ በማድረግ ረገድ ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

