ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላተ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ክፍል -1

ሀገራዊ ሪፎርምና ጠንካራ የኢኮኖሚ ስርዓት ግንባታን በተመለከተ በዓለም ላይ እየተፈጠረ ባለው የንግድ ስርዓት መዛባት፤ እንዲሁም በዋና ዋና ምርቶች ላይ ባጋጠመው የምርት እጥረትና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪና የእድገት መገራገጭ አጋጥሟል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ሲከናወን በቆየው የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራ ምክንያት ፈተናዎችን የሚቋቋም አቻዮ የኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት ችለናል። የኢኮኖሚ መልሶ ክለሳን በተመለከተ ባለፉት…

የነዳጅ ዋጋ በሊትር ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አንጻር

ኬኒያ —-1 ነጥብ 7 ዶላር ጂቡቲ —-1 ነጥብ 77 ዶላር ኡጋንዳ —– 1 ነጥብ 57ዶላር ታንዛኒያ —– 1 ነጥብ 53 ዶላር ሩዋንዳ ——1 ነጥብ 99 ዶላር ኢትዮጵያ —–1ነጥብ 04 ዶላር

ወደብ ሳይኖረን፣ የነዳጅ ዴፖ ሳይኖረን

ወደብ ሳይኖረን፣ የነዳጅ ዴፖ ሳይኖረን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠመውን የነዳጅ ቀውስ ለመቋቋም በከፍተኛ ድጎማና ነዳጅ ቁጠባ ያከናወነው ስራ ምስጋና የሚቸረው ነው። በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ነዳጅ በድጎማ ማምጣት ብቻ ሳይሆን ያስተዳደርንበት መንገድ ከፍተኛ ምስጋና የሚቸረው ተግባር ነው።

የወጪ ንግድን በተመለከተ

ከወጪ ንግድ አንጻር ባለፉት ሶስት ወራት 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ከወጪ ንግድ ማግኘት ተችሏል። ይህ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ25 በመቶ እድገት አለው። ከሀገራዊ ሪፎርሙ በፊት ካሉ ዓመታት ጋር ካነጻጻርነው ደግሞ የአንድ ዓመት የወጪ ንግድ ገቢ ጋር የሚስተካከል ነው። ይህ ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም እያላት በአሰራር ውስንነት ተይዛ እንደነበር የሚያሳይ ነው።

የዲጂታል ፋይናንስን በተመለከተ

በኢትዮጵያ የባንኮች ተቀማጭ 5 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር ደርሷል። አጠቃላይ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥርም 70 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን በኢትዮጵያ 11 ትሪሊን ብር በዲጂታል ፋይናንስ ይዘዋወራል። ይህም በተለይ የብድር አቅርቦትን ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ አቅም ፈጥሯል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን በተመለከተ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረበት 2 ነጥብ 6 ትሪሊዮን ሃብት ዛሬ 9 ትሪሊዮን ደርሷል። ትልቅ ይወድም የነበረ ሃብተን በማሰባሰብ አጠቃላይ ሃብቱን በሶስት እጥፍ ማሳደግ ችሏል። ከገቢ አንጻርም አሁን ላይ 3 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር ያስገባል። ባለፉት 3 ወራት ብቻ 72 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ተችሏል። ይህም የመንግስት ሃብት ከመበዝበዝ ወጥቶ ትርፍ…

የግብር መሰረት ማስፋትን በተመለከተ

ኢትዮጵያ ውስጥ የግብር መሰረትን የማስፋት ስራን በደንብ ማየት ይገባል። በርግጥ ግብር መክፈል ክብር ነው። ሁሉም ዜጋ ይህን በደንብ መገንዘብ አለበት ። ታማኝ ግብር ከፋዮች አሁንም በጣም ጥቂት ናቸው። ከጥቅል ዓመታዊ ምርታችንም አንጻር የሚሰበሰበው ግብር በጣም ትንሽ ነው። ስለዚህ ይህን በአሰራርና በህግ ማስተካከል ይገባል።

ኢንዱስትሪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና የተሻለ ድርሻ መያዝ ችሏል!

ኢንዱስትሪ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከግብርና የተሻለ ድርሻ መያዝ ችሏል! ግብርና ከጥቅል ዓመታዊ እድገታችን 31 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ አለው። ኢንዱስትሪ ደግሞ 31 ነጥብ 8 በመቶ ድርሻ በመያዝ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጥቅል ዓመታዊ እድገታችን ከግብርና የተሻለ ድርሻ መያዝ ችሏል። ይህ እንግዲህ ኢንዱስትሪው በፍጥነት እያደገ መሆኑን የሚያመላክት ነው።

የኢትዮጵያን ጥቅል ዓመታዊ ምርት በሚመለከት

የኢትዮጵያን ጥቅል ዓመታዊ ምርት በሚመለከት በኢኮኖሚ ክለሳው መሰረት የኢትዮጵያ ጥቅል ዓመታዊ ምርት 210 ቢሊዮን ዶላር በመሆን ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት 3ኛው ትልቁ ኢኮኖሚ መሆን ችሏል። ይህ ሂደት በጥብቅ ዲሲፕሊን የተመራ ነው።

የባቡር መሰረተ ልማትን በተመለከተ

የባቡር መሰረተ ልማትን በተመለከተ የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ኮርፖሬሽንን ለማሻሻል በተከናወኑ ስራዎች ከዚህ በፊት ይገኝ የነበረውን ትርፍ ከ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወደ 43 ቢሊዮን ብር ማሳደግ ተችሏል። የነበሩትን ሎኮሞቲቮችን ከ11 ወደ 36 ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፤ አሁን ላይ ከአንድ ሺህ በላይ ጋሪዎችንም ማስተዳደር ችሏል። የመንገደኞችን አገልግሎትም ከ198 ሺህ ወደ 588 ሺህ አሳድጓል። ከጋርጎ አንጻርም ወደ 4…