ኢትዮጵያዊነት በኅብር ቀለም!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ኢትዮጵያዊነትን የገለጹበት መንገድ የመደመር ፍልስፍና መሠረት ሲሆን ኢትዮጵያዊነትን በአንድ ወገን ወይም በአንድ ቀለም ሳይሆን፣ በሁለንተናዊ የኅብረት ስብስብ መልክ አስቀምጠዋል። “ኢትዮጵያዊነት በኅብር ቀለም የሚሳል፤ በኅብር ባህል ሚኖር፤ በኅብር ቋንቋ የሚነገር፤ በኅብር ደም የተሠራ፤ በኅብር ላብ የሚገነባ፤ በኅብር ጥበብ የሚሻገር” የሚለው ሐሳብ፣ ብዝኃነትን እንደ ስጋት ሳይሆን እንደ ጥሬ ኃይል (Raw Power) ያሳያል። እያንዳንዱ…
“የኔነት” ሳይሆን “የኛነት”
የኢትዮጵያ ባህላዊ ሀብት እንደ ብሔራዊ መደመር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት ይህ አጭር ግን ጥልቅ መልእክት፣ የኢትዮጵያን ባህላዊ፣ ታሪካዊና ማኅበራዊ እሴቶች ከጎጥ ወሰን በላይ ያለውን ዋጋ ያሳያል። መልእክቱ የኢትዮጵያዊነትን ትርጉም ከነጠላ ማንነት ወደ የጋራ ንብረትነት በማሸጋገር የብልፅግናን ራዕይ ይደግፋል። ብዝኃነት እንደ የጋራ ሀብትና ባለቤትነት፣ ይህ መልእክት እያንዳንዱ ክልላዊ ወይም ብሔረሰባዊ እሴት ለአንድ ብሔረሰብ ብቻ…
የብሔር፣ ብሔረ-ሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሕገ መንግሥታዊ ቃል ኪዳናችንን የምናድስበትና የብዝኃነታችንን ዐቅም የምናልቅበት ቀን ነው!
ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የሚገለጽ ብዝኃነት ባለቤት ናት፡፡ የቋንቋ፣ የባህል፣ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ የፖለቲካዊ አመለካከት፣ የዕድሜ፣ የፆታ ወ.ዘ.ተ ብዝኃነቶቿ የሚያስጌጧት ድንቅና ቀደምት ሀገር ናት፤ ኢትዮጵያ፡፡ ይህንን ብዝኃነቷን እንደ እሴት የምታዳብርበት፣ እሴቱን ወደ መፈጸም ዐቅም የምትለውጥበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐት ባለቤትም ናት፡፡ ለዚህም ነው የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ በሆነው ሕገ መንግሥታችን አንድ የጋራ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት በነፃ…
“ኢትዮጵያ ታላቁ ሕዳሴ ግድብን በራስ ዐቅም ገንብታ ማጠናቀቋ ለአፍሪካ ሌላ ዐዲስ ምዕራፍ ነው፡፡” የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኞችና የቀድሞ የፍሪካ መሪዎች ቤተሰቦች
ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ የቀድሞ ፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ መሪዎች ቤተሰቦች እና ጋዜጠኞች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በሰጡት አስተያየትም “ኢትዮጵያ ፓን አፍሪካኒዝምን በላቀ መሠረት ላይ ገንብታዋለች፤ ይህ ለአፍሪካ ሌላ ዐዲስ ምዕራፍ ነው” ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያውያን በራስ ዐቅም እና ጥረት የተገነባዉ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከዓድዋ ድል እና ከአፍሪካ ኅብረት ምሥረታ ቀጥሎ ሦስተኛዉ የፓን አፍሪካኒዝም መሠረት…
የጋራ አህጉር ለጋራ አላማ!
ታላቋ አፍሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪኳን በራሷ ብዕርና ድምፅ ለመጻፍ የገበየችበትን የፓን-አፍሪካ የሚዲያ ሽልማት (AMA) ለማስተናገድ የተመረጠችው አፍሪካዊት መዲናችን አዲስ አበባ፣ የላቀ ሃላፊነቷን በብቃት እየተወጣች ትገኛለች። በመላ አፍሪካ ርዕሰ ከተሞች መካከል፣ ለዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲና የጋራ አህጉራዊ ተቋማት ማዕከል በሆነችው ምድራችን፣ ይህን ታላቅ የሚዲያ መድረክ ማስተናገድ ታላቅ ኩራት ነው። የአፍሪካ ሕብረት መናኸሪያ፣ የዲፕሎማሲና የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል…
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የራስን ሀብት በራስ ዐቅም ማሳካት እንደሚቻል የሚያሳይ ዐዲስ የፓንአፍሪካኒዝም አብነት ነው፡- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ታላቁ የኢትዮጵያ ግድብ ከኃይል ማመንጫ ግድብነት ባሻገር በራስ ዐቅም የራስን መሻት ማሳካት እንደሚቻል ያሳየ ዐዲስ የፓን አፍሪካኒዝም አብነት መኾኑን የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትር ዲኤታዉ አርቲ አፍሪካ ባዘጋጀዉ የአፍሪካ የሚዲያ ዕውቅና መድረክ ዋዜማ ላይ ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካኒዝም ማእከልነቷን ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በራስ ዐቅም በማሳካት እንደገና ማስቀጠሏን አመልክተዋል፡፡…
